ታላቅ ክብ በጂዎሜትሪ ማለት በማንኛውም ሉል ላይ ከሁሉ ትልቅ የሆነው ክብ ማለት ነው። እንዲያውም በሉሉ ላይ የሆኑት የታላቅ ክቦች ቁጥር ያልተወሰነ ነው። ክቡም ሉሉን በግማሽ ይለየዋል። በሉሉም ገጽ ላይ በማናቸውም 2 ነጥቦች በኩል የሚሄድ አጭሩ መስመር ሁሉ ታላቅ ክብ ላይ ይሆናል። ስለሆነም ታላቅ ክብ የሉል ጂዎዴሲክ ይሰኛል።